ትንሹ “ኒቼ ኤስ” አንድሮይድ ስማርት ስልክ ለገበያ ሊቀርብ ነው

በአሁኑ ጊዜ በገበያ ላይ ብስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ስማርት ስልኮች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተለቀ መጥቷል። ኒቼ ኤስ የተባለው አንድሮይድ ስማርት ስልክ ግን መጠኑን ቀንሶ መጥቷል ነው የተባለው።
በጃፓኑ ኩባንያ የሚሰራው አዲሱ አንድሮይድ ስማርት ስልክ “ኒቼ ኤስ” የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፥ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀም ነው። የስማርት ስልኩ መጠንም ከኤቲኤም ካርድ ጋር እኩል ነው የተባለ ሲሆን፥ በርካታ ነገሮችን ለመከወን ያስችለናልም ተብሏል። ከእነዚህም ወስጥ ስልክ መደወል፣ የፅሁፍ መልእክት መላላክ እና ሙዞቃ ከኢንተርኔት ላይ ለማዳመጥ ይገኙበታል።

ስማርት ስልኩ ከሶስት ቀን በኋላ ጥቅምት 30 ቀን በጃፓን ለገበያ ይቀርባል የተባለ ሲሆን፥ የመሸጫ ዋጋውም ርካሽ መሆኑ ነው የተነገረው። የአንድ ኒቼ ኤስ አንድሮይድ ስማርት ስልክ የመሸጫ ዋጋም 95 የአሜሪካ ዶላር ተቆርጦለታል ነው የተባለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *