አትሌት አልማዝ አያና በዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ምርጫ የመጨረሻዎቹ 3 ሴት እጩ አትሌቶች ውስጥ ተካታለች

አትሌት አልማዝ አያና በዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ምርጫ የመጨረሻዎቹ 3 ሴት እጩ አትሌቶች ውስጥ ተካታለች

አትሌት አልማዝ አያና የ2017 በዓለም ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ ሶስት ምርጥ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ገብታለች።

ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በዛሬው እለት በሴቶችና ወንዶች የዓመቱን ምርጥ 3 ዕጩ አትሌቶች ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በለንደን በተካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችው አትሌት አልማዝ አያናም በሴቶች ምድብ ከተመረጡት ሶስት ሴቶች ውስጥ አንዷ ሆናለች።

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በሴቶችና ወንዶች የዓመቱን ምርጥ 3 ዕጩ አትሌቶችም፦

በሴቶች
አትሌት አልማዝ አያና ከኢትዮጵያ
አትሌት ኤካትሪኒ ስቴፋኒዲ ከግሪክ
አትሌት ኒፋሳቶ ቲሃም ከቤልጂየም

በወንዶች
አትሌት ሞህ ፋራህ ከእንግሊዝ
አትሌት ሙታዝ ኢሳ ብራሺም ከኳታር
አትሌት ዋይዲ ቫን ኒዬኬርክ ከደቡብ አፍሪካ ሆነዋል።

የ2017 በዓለም ምርጥ አትሌት ምርጫ ቀጣይ ሂደትም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ምክር ቤት፣ አባላት እና በህዝብ (በደጋፊዎች) በሚደረግ ድምፅ አሰጣጥ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል።

ይህም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ካውንስል ድምፅ 50 በመቶ ድርሻ ሲኖረው፤ የአባላት እና የህዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዱ 25 በመቶ ይይዛል።

የአመራረጥ ሂደቱም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ካውንስል እና አባላት ድምፃቸውን በኢ ሜይል የሚሰጡ ይሆናል።

የህዝብ (የደጋፊዎች) ድምፅ ደግሞ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የማህበራዊ ድረ ገፆች አማካኝነት ነው የሚመርጡት።

በአጠቃላይ የውድድሩ አሸናፊም ህዳር 15 ቀን 2010 በሚካሄድ ስነ ስርዓት የሚታወቅ መሆኑን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ድረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ባለፈው አመት በሴቶች አልማዝ አያና በወንዶች ደግሞ ጃማይካዊው ዩዜን ቦልት የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች በመባል መመረጣቸው ይታወሳል።
ኢቢሲ፣ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *