ኡበር እና ናሳ በራሪ ታክሲዎችን ለመስራት ስምምነት አስረዋል

ጥቅምት 30 ፣ 2010 (ግዕዝ ሚዲያ) በተለያዩ ሃገራት የከተማ ታክሲ አገልግሎት የሚሰጠው ኡበር ኩባንያ በራሪ ተሽከርካሪዎችን ለመስራት ስምምነት ፈጽሟል።
ኩባንያው ከአሜሪካው የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ጋር ነው ስምምነቱን የፈጸመው ተብሏል።
ስምምነቱ በትልልቅ ከተሞች በራሪ ታክሲዎችን ለማሰማራት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያለመ ስለመሆኑም ነው የተነገረው።
አሁን ባለው ስምምነት ኡበር በራሪ ታክሲዎችን አይሰራም፥ ከዚያ ይልቅ ይህን ስራ ከሚሰሩ ኩባንያዎች ጋር ሌላ ውል ያስራል ነው የተበላው።
ለዚህም ፒፒስትረል ከተባለው ኩባንያ ጋር እንደሚሰራ ኩባንያው በድረ ገጹ ላይ አስነብቧል።
በተጨማሪም በሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ላይ ለታክሲዎቹ ማረፊያ የሚሆን ስፍራ ከአንድ ኩባንያ ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ገልጾም ነበር።
ከዚህ ባለፈ ግን የበራሪ ታክሲዎችን አጠቃላይ መንገድና እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችለውን ቴክኖሎጅ ኩባንያው ራሱ የሚሰራ  ይሆናል።
ለዚህ የሚረዳውን ሶፍትዌርም በራሱ አማካኝነት እንደሚከውን ገልጿል።
የዘርፉ ባለሙያዎች ግን በአሁኑ እቅድ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፤ መሰል አካሄዶች ገበያን ለመሳብ ከማሰብ የመነጩ እንጅ በእውነታ የሚተገበሩ እንዳልሆኑም ነው የሚጠቅሱት።
ለዚህም ኩባንያው በተለያዩ ትልልቅ ከተሞች በሚሰጠው የከተማ ታክሲ አገልግሎት ያገጠሙትን ተደጋጋሚ ቅሬታዎች በማሳየነት ይጠቅሳሉ።
ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር እንዲሁም ከክፍያና መሰል ጉዳይች ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ እሰጥ አገባዎች ውስጥ ገብቶ ነበር።
አሁን ላይ ከናሳ ጋር እተገብረዋለሁ ባለው አሰራር ግን ይህን መሰሉ አጋጣሚ እንደማይደገም ነው የገለጸው።
ኡበር ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2020 በዳላስ እና በዱባይ በራሪ ታክሲዎቸን አገልግሎት ላይ ለማዋል እየሰራ መሆኑ ይነገራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *