የጥቅምት ወር የቡና ግብይት ዋጋ በ58 በመቶ አደገ

በጥቅምት ወር የቡና ግብይት ዋጋ በ58 በመቶ ማደጉን የኢትዮጵ ምርት ገበያ አስታወቀ።
በዚሁ ወር አጠቃላይ የምርት ግብይት ዋጋውም 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ነው ያስታወቀው።
ምርት ገበያው ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫው በተጠናቀቀው የጥቅምት ወር በ22 የግብይት ቀናት ከ 37 ነጥብ 2 ቶን በላይ ምርት በ 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር አገበያይቷል።
በወሩ ከ27 ቶን በላይ ቡና ፣990 ቶን ቦሎቄ ፣ 8 ሺህ 990 ቶን ሰሊጥና 30 ቶን ማሾ ምርት ገበያው ያገበያየ ሲሆን ቡና ከአጠቃላይ የግብይት መጠን 73 በመቶ ከግብይቱ ዋጋ ደግሞ 87 በመቶ በማስመዝገብ በዚህ ወር ቀዳሚነቱን ይዟል።
በወቅቱ ግብይት የቡና ዋጋ በ8 በመቶ የጨመረ ሲሆን ከመስከረም 2010 ዓ.ም ግብይት ጋር ሲነጻጸር አጠቃላይ የግብይት ዋጋና መጠኑ እንደ ቅደም ተከተላቸው በ58 በመቶና በ68 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተገበያየው የቡና መጠንና ዋጋ ከእጥፍ በላይ የጨመረ ሲሆን ከአጠቃላይ ግብይቱ  ወደ ውጭ የሚላክ ቡና በቀዳሚነት እየመራ መሆኑም ተመልክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *