መከላከያ ሰራዊቱን ለቀቅ!!

(ባሻ ደስታ እንደፃፈው)

የፈሩት ይነግሳልና አዙሮ ማሰቡ አይከፋም!
. . . . .( መከላከያ ሰራዊቱን ለቀቅ). . . . . . .
= = = = = = = = = = = = = = = = = = = = =

እንዳንድ ለመምራት ቀርቶ ለመመራት እንኳን እማትመቹ “አመራር” ተብዬውቸ የሰው ትዕግስት አትጨርሱ!

ትንሽ አዙሮ ማሰብያ አልሰጣችሁም እንዴ?. . . ማን ላይ ምን ማውራት እንዳለባችሁ አታውቁም?. . . መቼ ምን እንደሚባል አትረዱም?

የሚገባችሁ ከሆነ እናንተ በምትመሩት ክልል በእናንተ ዝርክርክነትና ስልጣን መራሹ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ብዙ ዜጋ እየሞተ ነው። ዩኒቨርስቲዎቻቹ ትምህርት ሳይሆን ጥላቻ የሚቀሰምባቸው ፣ ፊደል ሳይሆን ዘር የሚቆጠርባቸው ፣ ሙሁር ሳይሆን ሬሳ የሚወጣባቸው የጦርነት አውድማ ናቸው። ይሄንን ያደረጋችሁ ጨካኝ አረመኔዎችና መቆጣጠር ያቃጣችሁ ዝርክርኮች አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ሌላው ላይ ለመጮህ ምን ዓይነት ሞራል ሊኖራችሁ እንደሚችል አላውቅም። . . . በቃ እስኪ ዝም በሉ – ትንሽ አታፍሩም እንዴ!

ጨለንቆ ላይ ሰው ሞተ – ሰው መሞቱ ያሳዝናል! ግን የእነዚህ ሰዎች መሞት ተጠያቂዎች እራሳችሁ “የእነዛ ሰዎች መሪወዎች ነን” ብላችሁ ለመቆርቆር የምትዳዱ መቼም በሰው ልጅ ሬሳና መጪ ህይወት ፖለቲካዊ ቁማራችሁን ለአፍታ ማቆም እማትፈልጉ አፈ ቀላጤ ቁማርተኞች ናችሁ። በእናታችሁ ትንሽ እፈሩ – ማፈር ባለብህ ሁኔታ ማፈር ኮ የኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ልባምነት መገለጫ ነው።

“እነዛ የተገየሉት ሰዎች ሕጋዊ/ሰላማዊ የመብት ጥያቄ እያቀረቡ እያሉ ነው – ሰልፉ ሰላማዊ ነበር። መከላከያ ሰራዊቱ በእነዚህ ሰላማዊ ሰልፈኞች ነው ሰልፍ የከፈተው።” ስትሉ ከጭንቅላታችሁ ተስፋ ብታስቆርጡን ምናለ አንገታችሁም ቢሆን አዙሮ ለማየት ብትጠቀሙበት! . . .ማፈርያ ሁላ! እነዛ ሰዎች ሰልፍ የወጡት ለሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄ ከነበረ – ጎዳና እስኪወጡ ድረስ ለምን መብቶቻቸውና ሕጋዊ ጥያቄዎቻቸውን አልመለሳችሁላቸውም???. . . ወይስ በእነሱ ሞት ለመነገድ ያዘጋችሁአቸው መደራደርያ ካርድ መሆናቸው ነው?? . . .ለማንኛውም “ለሟቾች መንግስተ ሰማያት ያውርስልን -ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን ይስጥልን”! . . . እናንተ ግን ለምስኪን ዜጎች የሞት ድግስ እየደገሱ “የለሁበትም” ማለት የትም አያስኬድም!

እንግዲህ ወደዳችሁም ጠላችሁም ከእናንተ በፊት የሚታሰርም ሆነ የሚጠየቅ አንድም የመከላከያ ሰራዊት አመራር አይኖርም – እስከመጨረሻ ህዝቡን እያደናገራችሁ ልትወራጩ ትችላላችሁ ግን “ከመሬት ስበቱ ሕግ ውጪ አይደላችሁም”. . . ዘላችሁ ዘላችሁ የቆማችሁበት ጋ ትመለሳላችሁ!

የመከላከያ ሰራዊቱ ነገር አሁንም ለራሳችሁ ስትሉ ለቀቅ አድርጉት። ኢህአዴግ አሁን በያዘው ስብሰባ የውስጥ መዥገሮችን ለማራገፍ እንደመጨረሻ አጋጣሚ ካልተጠቀመበት – ምድረ አዙሮ እማያስብ ነፈዝ ከመከላከያ ሀይሉና ከፌዴራል ፖሊስ የያዘው Phobia ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ሊያውቅ ይገባል። በሰላማዊና ሲቪል አመራር ሀገር ማረጋጋት ካቃጠህ ወደድክም ጠላህም የማትወደው ነገር ይመጣል። . . . በትዕግስቱና በህዝባዊ ዲሲፕሊኑ ሁሉም እየታዘበ ያለው የመከላከያ ሰራዊት እጁ ውሀ አልዘገነም! . . .የሰላም ዋጋ ለማይገባው ነውጠኛ ፖለቲከኛ ባርያ ሆኖ ሊያገለግል አይደለም በቃለ መሓላው ራሱን ለመስዋዕትነት ያዘጋጀው። አርፋችሁ ማትቀመጡ ከሆነ ለህዝቡ ደህንነትና ለአገሪቱ ህልውና ሲባል መከላከያ ሰራዊቱ “መፈንቅለ መንግስት” እስከማካሄድ ይደርሳል። ይህ መንግስት ሲፈነቀል እያንዳንድሽ አሁን ህዝብን እያደናገርሽ ያለሽው አፈ ቀላጤ አመራር በአፍ ጢምሽ ትደፊያለሽ። እሱም ብቻ አይደለም እየተለቀምሽም ተገቢውን ፍርድ ታገኚያለሽ!

ስለዚ እምትሉትን እወቁ – የሰውን ትዕግስት አታስጨርሱ – ህዝቡን በስሙ አትነግዱበት – ፖለቲካዊ ቁማራችሁን አቁሙ። አለበለዚያ ነገሩ “የጠሉት ይነግሳል ” እንዳይሆንና – እናንተን ፈጥሮ በገዛ ራሱ የመዋቅሩ አመራሮች እየተንገዳገደ ያለ መንግስት ተከርብቶ መከላከያ ሰራዊቱ ገዢያችሁ እንዳይሆን። ስለዚ ፖለቲካዊ ንትርካችሁን በሰለጠነ መንገድ ተግባብታችሁ ለመፍታት ዝግጁ ካለልሆናችሁ – የነገ ገዢያችሁ ላይ እጅ ባትቀስሩ ለራሳችሁ መልካም ነው።

ደግሞ ይሄንን ፅሑፍ አንብባችሁ በፍርሐት መንበጫበጭ ዋጋ የለውም – ለህዝቡ አስባችሁ ለሰላምና መረጋጋት ከልባችሁ ከሰራችሁ አሁንም አልረፈደም። አይ ያላችሁ እንደሆነ ግን ቀጣፊዎችን ሰዶ የማሳደዱ ስራ በይፋ ይጀመራል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *