የተጋሩ ታማኝነት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ልብ ኣይታጣም!

(ልፍዓተይ ተስፋ እንደፃፈው)
(ከተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች የሃገር ውስጥ ገጠሞቼ ጥቂቶቹ)

በ2008 ዓ/ም ከሓምሌ 23 – 30ባሉት ቀናት በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሳላማጎ ወረዳ ዋና ከተማ ሃና ሙርሲ በስተ ደቡብ ግዙፉ የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ #1 – 5ን ጎብኝቻለሁ። ከጂንካ ወደዚሁ ኣከባቢ ስትሄድ ተፈጥሮን እያደነቅ መሄድህ ግድ ቢሆንም (የማጎ ብሄራዊ ፓርክ ፤ የቦዲ ፤ የሙርሲ ፤ የባጫ ፤ ዲሜ ብሔረሰቦችን የማየት ዕድሉ ኣለ) ፤ በፀጥታው ደህንነት በኩል ግን ዋስትና የለም። በዚህ የስኳር ልማት ፋብሪካ ውስጥ ከሁሉም የሃገሪቱ ብ/ብ/ሰቦች የተውጣጡ የቀን ፡ የኮንትራት እና ቋሚ ሰራተኞች ኣሉ። ሰራተኞቹ ዓርብ ከ 11፡00 ሰዓት በኋላ እስከ እሁድ ከ 11፡00 ሰዓት በኋላ በስራ የተወጣጠረው መንፈሳቸውና ኣንዳንድ የምግብ ኣስፌዛ ለመሸማመት ጂንካ ከተማ ይሄዳሉ። በዚህ ጊዜ የኣከባቢው ነባር ነዋሪዎች የማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ኣስገድደው በማስቆም እነሱ እስከፈለጉበት ድረስ ይጓዛሉ። የሹፌሩ ግንባር ላይ በ”11″ ወይም በ”+” ምልክት የተበጣ ፤ ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት የፖሊስና የመከላከያ ተሽከርካሪ ካዩ ግን “ትግር” በማለት ሳይነኩህ መንገድክን በሰላም ትጓዛለህ።

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ከፊንፊኔ ክ/ከተማዎች መካከል እጅግ የናጠጡ የጎጃምና የጎንደር ቱጃሮች ሳይቀሩ ካለሰዓት ገደብ እና ካለስጋት የሚዝናኑበት ቦሌ ኣልያም ለገሃሬ ኣከባቢዎች ሳይሆኑ የ22 እና የካዛንቺስ ኣከባቢዎች ናቸው። በኣንፃሩ የለገሃሬ ኣከባቢዎች ሳይሆኑ የ22 እና የካዛንቺስ ኣከባቢዎች ብዙ ፖሊስ ያልተመደበበት ኣካባቢ ነው። ለምን? ብላችሁ ያገኛችሁትን ሰው ኣልያም እንደ ኣነፍናፊ ውሻ በቤቱ የሚጮህ ማንም ሰው ብትጠይቁ “የእነ እንትና ሰፈር ነው” የሚል መልስ ታገኛላችሁ?

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ጎንደር ማራኪ በ2002 ዓ/ም ኣባት ንስሃ ልንይዝ በ 1 ዶርም የምንኖር 8 ተማሪዎች ነን። 2 ከጎጃም ፡ 1 ከደሴ ፡ 3 ከኦሮሚያ(1ዱ ጴንጤ) ኣንዱ ጉራጌ ነበርን። 7ታችንም ኣባት ንስሃ ልንይዝ ወደ ቀሃ እየሱስ ልናመራ ተስማምተን ስናበቃ የጎጃምና የወሎ ልጆች ወደ ኣራዳ ኢየሱስ ቤ/ክ እንሂድ ብለው ተጫኑን። ለምን? ብንላቸው “እዚህ የትግራይ ካህን ኣናገኝም” ብለውን እርፍ?

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ኣዳማ ለስብሰባ ሂደን ማያ ሆቴል/ኣሁን ኩሪፍቱ ሪዞርት ሆኗል/፤ ወቅቱም ሚያዝያ 2007 ዓም ነበር። ኣብረውኝ የሚሰለጥኑ ጓደኞቼም እዛው የተዋወቅኩት 2 የኣማራ ልጆች ነበሩ። ስልጠናው ሊጠናቀቅ የ1 ቀን ዕድሜ ሲቀረው 1ዱ የኣማራ ልጅ ድንጋጤ በተሞላበት ሁኔታ “እባክህን በዚህኛው የኣካውንቴን ቁጥር የሚሰጡኝን የስልጠና ኣበሌን ኣስገባልኝ” ኣለኝ። “ኣብሮህ የመጣውን ጓደኛህን ብትለው ኣይሻልም?” ኣልኩት። እሱም መልሶ “ትግሬ ነኝ ያልከኝ መሰለኝኮ” ኣለኝ። እኔም ገባኝና ተቀበልኩት። ለካ ያባቱን ሞት መርዶ ላይ ሆኖ ነበር የህሊናውን እውነት ያበሰረኝ?

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

የዛሬ 2 ወር ገደማ ባህርዳር ፓፒረስ ሆቴል ነበርኩኝ። ከ3 ቀን ቆይታ ከሆቴሉ ፊት ለፊት ኣንዲት ትንሽዩ ካፌ ማሟሻየን እየኮመኮምኩኝ ነው። ከፊት ለፊቴ ትልቅ ኣባት ኩታ ለብሰው የክልሉን TV እያዩ ኖሯል። ዜናው “ኣማርኛን ቋንቋ በሃገሪቱ የምርምር ቋንቋ ለማድረግ የባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ እየሰራ ነው” ይል ነበር። እሳቸውም ፈገግ ኣሉ ፤ እኔ ደግሞ “ምነው ኣይቻልም እንዴ?” ስል ጠየቅኳቸው። እሳቸውም “ልጄ እሱስ ይቻላል ፤ ነገር ግን የኣማርኛን ቋንቋ የኣማራው ማንነት ያጠና እንደሆነ እንጂ ግእዝና ትግረኛ በሚነገርባት ኢትዮጵያ እንዴት ሆኖ ነው ኣማርኛን ቋንቋ በሃገሪቱ የምርምር ቋንቋ ለማድረግ የሚቻለው?” በማለት ጥያቄየን በጥያቄ መለሱልኝ።

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ግንቦት 16/2008 ዓ/ም ለኔ ደስ የሚል ቀን ነበረ ፤ በወላይታ ዞን ፤ የበሎሶ ሶሬ ወረዳ መቀመጫ የሆነቺው የኣረካ ከተማ በፍጥነት እየጎመራች ትገኛለች። ኣየሯ ተስማሚ ነው። ብዙ ሰዎች የጠ/ሚ ሓ/ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ የኣረካ ከተማ ይመስላቸዋል ። የሳቸው የትውልድ መንደር ግን ከኣረካ ከተማ 7 ኪ/ሜ ርቃ በምትገኘው የ “ቦምቤ” ቀበሌ ነው። በዚህች ቀበሌ የሚበዙትን የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ለፃድቁ ኣቡነ ተክለሃይማኖት ልዩ ፍቅር ኣላቸው። የሰዎቹ መጠርያ ስምም እንደ ተጋሩ ስም ነው። በዚህች ቀበሌ የሚኖሩ የዱቦ ፤ የቦምቤ እና የኣጆራ ፏፏቴ ኣከባቢ ሰዎች በኣፄ ዳዊት 2ይ ፤ በልብነ ድንግል እና በዘራ ያቆብ ዘመን ከትግራይ መጥተው እንደሰፈሩ ይናገራሉ። በሳይንሳዊ/ታሪካዊ ጥናትም ተረጋግጧል። ጠቅላያችንም የነዚህ ዘር ናቸው።

https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_rulers_of_Welayta List of rulers of Welayta – Wikipediaen.wikipedia.org

ታድያ ወደነዚህ ሰዎች ስትሄድ ትግራይ ነው ኣገሬ ብትላቸው ከቤተሰባቸው ይቆጥሩሃል።

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ወቅቱ 1988 ዓ/ም ፤ ቦታው በኦሮሚያ ክልል ምስ/ወለጋ ዞን በኣንገር ጉቲን ከተማ ዙርያ መንደር 11(ኣባ ሙሳ ቀበሌ) ነው ። በተፈጥሮ የተቸረው ሰፊውና የተንጣለለው ኣውላላው ሜዳ ሁሌም የጉንበት ወር በገባ በ15ኛው ቀን በግብርና መኪና “ትራክተር” ይታረሳል ፤ በዘመናዊው የመሬቱ ማለስለሻ “መከሽከሻ” ይደገማል። ይህ የዚያ ኣከባቢ ኢትዮጵያውያን ከባህላዊ ግብርናም የተሻለ ፡ ወደ ሙሉ የግብርና ቴክኖሎጂም ገና ያልተሻገረ የኣሰራር ዘያቸው ነው። ቡቅያቸው ደግሞ የ120 ቀኗ ፈጥኖ ደራሽ ምርጥ የበቆሎ ዘር /Extension Maize/ ሲሆን ሓምሌ በገባ ከመጀመሪያው ሳምንት ጀምሮም ከባለ4 ኣንጓው የበቆሎው ስር ነጭ ፤ ቀይና ጥቁር ቦለቄ ያፈናጥሩበታል። ታድያ ትግራዋይ ያልሆነው ባለ ሃብቱም/Investor/ ጭምር እህሉን የሚያስኮተኩተው ፤ የሚያሳርመው እና የሚያሰበስበው በጎጃሜዎች ፤ በጎንደሬዎችና በተጋሩ የቀን ሰራተኞች ሲሆን ምርቱን የሚያስጠብቀውና የሚያስወቃው ግን በተጋሩ የቀን ሰራተኞች ነው። ይህ ማድረግ ካልቻለ ደግሞ የቀን ሰራተኞቹን የሚቆጣጠሩ ተጋሩ ሸቃዮችን በባትሪ ይፈልግ ዘንድ ይገደዳል። የሚገርመው ግን ይህ ብቻ ሳይሆን ጎጃሜዎቹና ጎንደሬዎቹ የቀን ሰራተኞችም ደመወዛቸው የሚያስቀምጡት በተጋሩ የስራ ቢጤዎቻቸው ላይ ነው። ተጋሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በላይ ይታመናሉ ፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለዘበኛና ቡክ ኣይታመንምና?

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

ነቀምቴ በኦሮሚያ ክልል የምስ/ወለጋ ዞን ዋና ከተማ ናት። ዘመኑ 1995 ዓ/ም ነው። ቤታችንን የተከራየንባቸው ሰዎች ስልጣን ላይ ላለው ስርዓት ኣምርረው የሚጠሉበት ዋናው ምክንያት በ1994ቱ የኣከባቢው ኣለመረጋጋት ወቅት ከቤተሰቡ 3ኛ ልጃቸው በፀጥታ ሃይሎች በመገደሉ ነው። ነቀምቴ 04 ቀበሌ /ማርያም ሰፈር (ኣፄ ዮሃንስ ያስሰሯት ጥንታዊት ቤ/ክ) በሰዎቹ ኣባባል መጤ ይበዛበታል። እናም በግርግር ወቅት ቀድሞ ኣይሳተፍም። ይህ የከተማው ኣከባቢ ሁነኛ መግባብያው ኦሮምኛ ኣይደለም ፤ ይሀው የምታነቡት እንጂ። እናም በ1995 ዓ/ም በጥባጭ ልጃቸው መቀለ ዩኒቨርሲቲ(FBE) ደረሰው።እናትየው በደስታ ብዛት ግቢውን በዕልልታ ቀወጡት ዘለሉ ፤ እንደ እምቦጭ ሳይሆን እንደ ደቦል ፈነጠዙ ፤ ቡሽሮ ድክድክ የቆመው ሆዳችንን እራት ላይ እንግዳው ቀይወጥ ቸለሰው ፤ ባጠቃላይ ፍሰሃ ወደስታ ሆኖ ኣመሸ። እኔ ግን ያልተዋጠልኝን ነገር የመጠየቅ ኣባዜ ኣለብኝና ሾፌሩ ኣባትየውን፦

እኔ፦ ጋሼ ፡

እሳቸው፦ ወየ፡

እኔ፦ ኣምና ቦንቱ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ይህን ያክል ያልተደሰቱ ዛሬ ግን ያስደሰትዎት ነገር ኣልገባኝም፡

እሳቸው፦ ኣየህ ፀጋዬ ቦንቱ ዘንድሮ ኣቋርጣ በሂይወት መምጣቷ ለኔ ትልቅ ደስታ ነው ፤ ምን ችግር ኣለው ቀጣይ ኣመት ትቀጥላለች ፤ የዚህ ልጅ ፀባይ እንደምታውቀው ዲንጋይና መስታወት ሲሰብር የሚውል ከንቱ ልጅ ነው ፤ እንደዛኛውም ልጅ እንዳይሞትብኝ ከስጋት ተገላገልኩኝ። እናም ዓመፅ የማይሰማበት ዩኒቨርሲቲ ስለደረሰው ቢያንስ ቢያንስ ባይመረቅም ከዚያ ታላቅ የትግራይ ህዝብ ኣኗኗር ስርዓትና ስነምግባር ተምሮ ይመጣል ኣሉኝ።

እውነት ለመናገር ስለተጋሩ መልካምነት በነገሩኝ ጊዜ በልቤ ኮራሁኝ። ደስስም ኣለኝ። ልጁ ተመርቆ ባሁኑ ሰኣት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኣምቦ የሁሉቃ ቅርንጫፍ ዋና ስራ ኣስኪያጅና የ 3 ልጆች ኣባት ነው።

<><><>>><><><><><><><>///<><><><><><>>><><><><><><>

እናም የተጋሩ ታማኝነት ለመናገር/ለመመስከር ባይፈልጉም በሁሉም ኢትዮጵያውያን ልብ ኣይታጣም 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *