የወልድያው ነውጥ እና የብአዴን ሴራ!

(ክብሮም ግደይ እንፃፈው)

እግር ኳስን ሽፋን በማድረግ በወልዲያ የታየው ኣሳፋሪ ነውጥ የብአዴን ትምክህተኛው ክንፍ ሴራ ነው!
ውልድያ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት ምንድን ነው?

-በወልድያ ኳስን ተገን አድርጎ የተከሰተው እውነተኛ ክስተት በአጭሩ ሲታይ ከጎንደርና ባህርዳር የተውጣጡ ትምክህተኞች ከብአዴን ትምክህተኛው ክንፍ የተሰጣቸውን ፖለቲካዊ ተልዕኮ ነው የፈፀሙት፡፡

-እነዚሁ ሃይሎች ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ከጎንደር ደብረዘይት ድረስ ሄደው ከአንዳንድ ጠባብ ሃይሎች ጋራ በማበር የእሬቻ በዓልን ማወካቸው ይታወሳል፡፡

-እነዚህ ሃይሎች በቀጣይም በተመሳሳይ የትግራይ ክለቦች ከኦሮሚያ ክለቦች ግጥሚያ በሚያደርጉበት ግዜም ወልድያ ላይ እንደፈፀሙት ዓይነት ተመሳሳይ ኣሳፋሪና አስፀያፊ ድርጊት ላለመፈፀማቸው ምንም ዋስትና የለም!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

-ኢህአዴግ ውስጥ ሆኖ ፀረ- ኢህአዴግ የቆመው፤የፌደራሉ መንግስት አካል ሆኖ ፀረ-መንግስት የቆመው፤በክልሉ በሚኖሩ ተጋሩ ላይ በተከታታይ ለዓመታት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን በስውር በማቀነባበር ላይ የተጠመደው የብአዴን ትምክህተኛው ክንፍ ነገር ሊለይለት ይገባል!

-በወልድያ ኳስን ሰበብ አድርጎ የተፈጠረው አሳፋሪ ድርጊት ድንገተኛ ሳይሆን ታስቦበትና ታቅዶበት የተፈፀመ ፖለቲካዌ ሴራ ነው!

-በአማራ ክልል ኳስን ሰበብ እየተደረገ በተደጋጋሚ በጎንደር፤ ባህርዳር አሁን ደግሞ በወልድያ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ያሉት ኢ-ሰብዓዊና ኣሳፋሪ ድርጊቶች ለረዥም ግዝያት ከዛሬ ነገ የፌደራሉ መንግስት መፍትሔ ያበጅለት ይሆናል በሚል ተስፋና ለስርዓቱ ካለው እምነት በመነጨ የትግራይን ህዝብ እስካሁን በትዕግስት በዝምታ ሲጠብቀ ኖራል፡፡

-ይሁንና በአማራ ክልል ኳስም ሆነ ሌሎች ምክንያቶችን ሰበብ እየተደረጉ በትግራይ ህዝብ የሚፈፀሙ ኢ-ሰብዓዊና ፀረ-ፌደራላዊ ስርዓት የሆኑ ድርጊቶች በመቆም ፈንታ እየተበራከቱ በመምጣታቸውና ከቅርብ ግዜ ወዲህም የሰው ሂወት ጭምር ወደ ማጥፋት ደረጃ በመሻገራቸው የትግራይ ህዝብ ለረጅም ግዝያት አምቆት የነበረውን ዝምታ ለመስበር ተገዶዋል፡፡

በመሆኑም፤
-የፌደራል መንግሰትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በአማራ ክልል ውስጥ በተደጋጋሚ እየተፈፀሙ ያሉና ሆኖ ተብሎ በክልሉ መንግስትና በፌደራሉ መንግስት ውስጥ በመሸጉ ትምክህተኛ የብአዴን ሃይሎች በአገር ውስጥና በውጭ ካሉ ተመሳሳይ ሃይሎች ጋር በመቆራኘት አየፈፀሙት ያሉት አንድን ዘር ማዕከል ያደረገ ጥቃትና የፌደራሉ ስርዓቱን የማፍርስ ድርጊት ከስሩ በመመርመር ከዚህ አሰፀያፊ ተግባር ጀርባ ያሉት መንግስታዊ ሃላፊዎች በህግ ተጠያቂ የሚሆኑበትን ስርዓት በማበጀት ለፍትህ ሊያቀርባቸው ይገባል፡፡

የብአዴን ትምክህተኛው ክንፍ በትክክለኛው ጥልቅ ተሃድሶ ሰይፍ ተቆርጦ ካልተጣለ፤
-በአማራ ክልል በሚኖሩ ተጋሩ ላይ እየተደረገ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት ይቀጥላል፡፡
-በአማራ ክልል እውነተኛ ሰላምና መረጋጋት ፈፅሞ አይሰፍንም!
-ከጠባብ ሃይሎች ጋር በማበር በፌደራል ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ ወደ ከፋ ደረጃ ይቀጥላል፡፡

-በአጠቃላይ ያገራችን ሰላምና መረጋጋት ፈፅሞ ጠፍቶ አገር ልትፈርስ የምትችልበት ሰፊ ዕድል ሊፈጠርም ይችላል፡፡

-ሁሉም ነገር ልክ አለውና፤ የትግራይ ህዝብ ትዕግስትም ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ በመሆኑ ያገራችን ህልውና ከመቼውም ግዜ በላይ ለፈተና ቀርቦዋል፡፡ ይህ ፈተና አገራችንን ለመፈራርስ ከመዳረጉ በፊት በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *