ይህች አገር ስንት ህግና ስንት መንግስት ነው ያላት?

(ክብሮም ግደይ እንደፃፈው)

የትግራይና የቅማንቶች ጉዳይ በአማራ ክልል

——————————————————-

-ከዓመታት በፊት በጎንደር ተከስቶ በነበረው ፀረ-ሰላም፤ፀረ-ፌደራላዊው ስርዓትና ፀረ-ብሄርብሄረሰቦች መብት ዓመፅ በርካታ የትግራይ ተወላጆችና የቅማንት ብሄር ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጥቃትም ወደ 20ሺ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ከጎንደር ከተማ፤ ከመተማና ሽንፋ አካባቢዎች ንብረታቸው ተዘርፈው፤ ተንገላተው ተፈናቅለው ወደ ሱዳን መሸሻቸው በአማሬካ ድምፅ ሬድዪ ጭምር ሽፋን የተሰጠው እውነት ነው፡፡

-እነዚህ የትግራይና የቅማንት ብሄር የነበሩት የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ለዓመታት ሲኖሩበት ቀየ መንግስትና ህግ ባለበት አገር ለጥቃትና ለስደት የተዳረጉት በትምክህተኛው የብኤደን ክንፍ ከጎንደር ህብረትና መሰል ትምክህተኛ ሃይሎች ጋር በማበር በተደረገ ዘረኛ፤ ኢ-ሰብዓዊና ኣሳፋሪ ድርጊት ነበር፡፡

-እነዚህ ወገኖች በተለያዪ አጋጣሚዎች ለብዙ ግዝያት የደረሰባቸውን ግፍ ለሚመለከተው አካል አቤት ለማለት ቢሞክሩም ሰሚ አላገኙም፤ አሁንም በተለያዪ አካባቢዎች ጥሬ እየተሰፈረላቸው እጅግ በጣም የሚያሳዝን ኑሮ በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡

-ይህንን እውነት ለማረጋገጥ በሁመራ የሚገኙትን የጥቃቱ ሰለባዎች ሁኔታ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

-እነዚህ ወገኖች ላይ የደረሰው ግፍ በተለያዪ ወገኖች በማህበራዊ ሚድያና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን መለስተኛ ሽፋን ካገኘ ወዲህ የፌደራሉ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍና ጥፋተኞችንም ለፍርድ ለማቅረብ እሰራለሁ ሲል ቃል ቢገባም እስካሁን መሬት የረገጠ የጥቃቱ ሰለባዎችን እንቢ የሚያብስ አንዳችም መፍትሔ አልተሰጠም! ተጠቂዎቹም አሁንም በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆነው በገዛ አገራቸው ተገፍተው የመከራ ኑሮን እየገፉ ይገኛሉ፡፡

የኦሮሞዎች ጉዳይ በሶማሌ ክልል

——————————————
-ባለፈው ዓመት አወዳይ ላይ በሶማሌ ብሄር ተወላጆች በጠራራ ፀሓይ በተፈፀመው አሳፋሪ የዘር ጥቃት(ሌሎች ጭፍጨፋ ይሉታል) የተነሳ የሶማሌ ህዝብና መንግስት ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም የክልሉ መንግስት 7 የሃዘን ቀናትን አውጆ የተጎጂዎችንም ስርዓተ ቀብር አስፈፅሞዋል፡፡

-የሶማሌ መንግሰት በአወዳይ በተፈፀመው ጭፍጨፋ የተነሳ በሶማሌ ህዝቦች ዘንድ የተፈጠረውን የተጠቂነትና ስሜት ወደ አላስፈላጊ የበቀል ድርጊት እንዳይቀየር በመስጋትና ይህ ቢከሰት በምንም መልኩ ሊቆጣጠረው እንደማይችል ሲያውቅ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ይህንን በግልፅ የሚታይን ስሜ በውል በመገንዘብ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የመሸሽ ፍላጎት ተደማምረው በርካታ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸው የሚታወቅ ነው፡፡

-የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ከሶማሌ ክልል መፈናቀል በወቅቱ በሶማሌዎች ዘንድ ተፈጥሮ ከነበረው መጥፎ ስሜት አንፃር ሲታይ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር የሚያስብል ነበር፡፡

-ከዚህ አንፃር የሶማሌ ክልል መንግስትም ሆነ ሌሎች አካላት በሰላማዊ ኦሮሞ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ከክልሉ ገለል እንዲሉ ያደረጉት ጥረት በቅንነት ከታየ እጅግ በጣም ሊመሰገን የሚገባው ፍፃሜ ነው፡፡

-እዚህ ላይ ይህንን እንዴት ሊመሰገን ይገባል የምትሉ ካላችሁ፤ ኦሮሞዎቹ በወቅቱ ከነበረው መጥፎ ስሜት አንፃር እንዲወጡ ባይደረግ ኑሮ አወዳይ ላይ ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት በላይ መጥፎ ክስተት ሊፈፀም የሚችልበት ሰፊ ዕድል እንደነበር ማሰቡ በራሱ ከበቂ በላይ ነው፡፡

-አሁን ነገሮች እየተረጋጉ በመምጣታቸውና በሶማሌዎች ዘንድ ተፈጥሮ የነበረው የተጠቂነትና የበቀል ስሜትም በተለያዪ ስራዎች እየበረደ በመምጣቱ የተፈናቀሉት ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ተወስኖ በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ ይህ እጅግ በጣም የሚያስደስት ነበር ነው፡፡ የሞተው አንዴ ላይመለስ ሞቶዋል፤ የተፈናቀለው ግን ግዜውን ጠብቆ ወደ ቀየው ተመልሶዋል፡፡

-ለዚህም ነው ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል እንዲወጡ የተደረጉበት ሁኔታ አገራችንን ከብዙ ጥፋት የታደገ ፍፃመ የነበረ በመሆኑ ከዚህ ጀርባ ያሉ ወሳኝ ሰዎች ሊመሰገኑ ይገባል የምለው፡፡

-የፌደራሉ መንግስት የትግራይ/ቅማንት በአማራ ክልልና የኦሮሞዎች በሶማሌ ክልል የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የሄደበት አካሄድ በዚች አገር ስንት ህግና ስንት መንግስት ነው ያለው የሚያስብል ነው፤

-በአማራ ክልል እጅግ በጣም ከላይ እስከ ታች ባሉት የአስተዳደር እርከኖች በተሰገሰቡ የስራ ሃላፊዎች በተቀነባበረ መልኩ ከከልሉ በተውጣጣ ሚሊሻ ጭምር በተደገፈ መልኩ በትግራይና በቅማንት ብሄር ተወላጆች ላይ የደረው በሰው ሂወት ላይ የደረሰ ጭፍጨፋ፤ በንብረት ላይ የደረሰው ውድመትና ዘረፋ እንዲሁም የደረሰው ከፍተኛ ሰብዓዊ መፈናቀልን ለመፍታት የፌደራሉ መንግስት የተጓዘው ርቀት እዚህ ግባ የማይባል ነው፡፡

-በተቃራኒው ግን ከኦሮሚያ ክልል ለደህንነታቸው ሲባል ለግዜው ከቀያቸው የተፈናቀሉትን የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ጉዳይ ለመፍታትና ነገሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ሲል የፌደራሉ መንግሰት የወጣውን አቀበትና የወረደውን ቁልቁለት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡

-ይህ በዓይነቱ ሁለት በስም ግን አንድ የሚመስለው የፌደራሉ መንግሰት ከልክም ልክ አልፎ በኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ የበቀል የዘር ጥቃት እንዳይፈፀምባቸው የሶማሌ ክልል መንግስት በማሰቡ በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮሞዎቹ በራሳቸው ከሁኔታው አንፃር ስጋት አድሮባቸው ከሶማሌ ክልል መውጣት በመፈለጋቸው መፈናቀሉ በመፈጠሩ ለዚህ ክስተት የሶማሌ ክልል ሃላፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ጭምር እየተውተረተረ ስለመሆኑ ስናስብ ነገሩ አጃኢብ ያሰኛል፡፡

መልዕክቴ
————-
-መልዕክቴ አንድና አንድ ነው፤ ይሀውም የፌደራሉ መንግስት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በትግራይና ቅማንቶች ላይ በአማራ ክልል መንግስት ውስጥና በፌደራሉ መንግስት በተሰገሰጉ ትምከህተኞ የብአዴን አመራሮች ውጭ አገር ካሉ ተመሳሳይ ትምክህተኞች ጋር በማበሩ ለፈፀሙትና ላስፈፀሙት ጭፍጨፋ፤ ሰብዓዊ መፈናቀል፤ የንብረት ዘረፋ ውድመት በህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ፍርድ እንዲያጉኙ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የነዚህ ግፈኞች ሰለባ የሆኑት ምስኪን ዜጎችም ተገቢውን ካሳ አግኝተው ወደ ነበሩት ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉት አሮሞዎች በተሰጠው ትኩረት ደረጃ ተገቢው ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ ይስጥ የሚል ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *