ወልዲያ- የድብቅ ሴራ ሰለባ!

(Jossy Romanat እንደፃፈው  )

ወልዲያ ውስጥ የተከሰተው ኣሳዛኝ ነገር መነሻ በጥምቀት በኣል ኣከባበር ላይ በተፈጠረ ድንገተኛ ግጭት ወይም በእግር ኳስ ጨዋታ ጊዜ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ብጥብጥና ቂም በቀል ሳይሆን ታስቦበትና ዝግጅት ተደርጎበት የተፈጸመ የኣመታት የጥላቻ ሴራና ዘመቻ ኣካል ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ መንገድ ኢህኣዴግን ማሸነፍ ያቃታቸው እነ ብርሃኑ ነጋ ከምርጫ 97 በኋላ ከኢትዮጵያ ሸሽተው ግንቦት 7 የሚባል ድርጅት ሲያቋቋሙ እንደ ብቸኛና የመጨረሻ የትግል ስልት ኣድርገው የያዙት “ትግራይንና ተጋሩን ነጥለህ መምታት” የሚለው ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የኢህኣዴግ ጥንካሬና ኣልሸነፍ ባይነት መሰረቱ የህወሓት ጥንካሬ ነው የህወሓት ጥንካሬ ሚስጥር ደግሞ የተጋሩ ድጋፍ ነው የሚል ድምዳሜ ነው፡፡ ይሄንን ትግራይንና ተጋሩን ነጥለህ የመታገል ኣላማና ስልት ለማሳካት እንደ ኣጋር የወሰዱት ደግሞ ሻእቢያን ነው፡፡ ሻእቢያም እንደ ግንቦት ሰባት ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ፈለግን መሆን ያልቻልነው በህወሓትና በተጋሩ ምክንያት ነው – በድንበር ጦርነቱ የተሸነፍነውም በተጋሩ ነው- ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ካለ ተጋሩ ተሳትፎና መሪነት እኛን ማሸነፍ ኣይችልም ነበር የሚል እምነት ኣላቸው – ይሄንንም በተደጋጋሚ ከድንበር ጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ በግልጽ ኣቶ ኢሳያስና ሌሎች የመከላከያ ባለስልጣኖቻው በሚድያቸው የገለፁት ነገር ነው፡፡ ታዲያ ይሄ ተጋሩ ላይ ያነጣጠረ የትግል ኣጀንዳ የቀረበላቸው ኣቶ ኢሳያስ ጥያቄውን በደስታ ተቀብለው ኣስተናገድውታል- ኢሳትን ጨምሮ በቂ ሃብትም ኢንቨስት ኣድርገውበታል፡፡

ግንቦት 7ቶች ኤርትራ ከገቡ በኋላ በ 2012 ኣካባቢ ለኣባላቶቻቸው በድብቅ ያሰራጩትና ያወያዩበት የትግል ሰነድ “ትግሉ ከተጋሩና ከትግራዋይነት” ጋር መሆኑን በግልፅ ያስቀምጣል – ይሄንን ኣጀንዳቸውም በተለያዩ ሚድያዎች ኣንጸባርቀውታል፡፡ በሻእቢያ ድጋፍ ባቋቋሙት ኢሳት በኩል በ”የትግራይ የበላይነት” ሰበብ ላለፉት በርካታ ኣመታት ትግራይንና ተጋሩን ዋና ኢላማ ኣድርገው ሰርተዋል፡፡ መሬት ላይ የሌለውን የትግራይ ተጠቃሚነት ኣጀንዳ በማራገብ ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ሰዎችን የጥላቻ ቅስቀሳ ሰለባ ኣድርገዋል፡፡ ኣጠቃላይ ተጋሩ ላይ በቴሌቪዥንና ሬድዮ በግልጽ የዘር ማጥፋት እወጃ እስከማወጅም ደርሰዋል፡፡

ግንቦት 7ቶች ለትግላቸው እንደ ደጀንና ቤዝ ኣድርገው የወሰዱትና ድጋፍ እናገኝበታለን ብለው ያሰቡት ለኤርትራ ቅርብ የሆኑ የኣማራ/ጎንደር ኣካባቢዎችን ሲሆን ይሄንን ኣካባቢ ለማነሳሳትም ላለፉት ኣመታት “ወልቃይትን ወሰዱብህ” የሚል በኢሳት በኩል ቅስቀሳ ሲያደርጉና “ትግሬ ገዳይ” እያሉ ሲሸልሉ ከርመዋል፡፡ በውጡቱም በወልቃይት ኣካባቢ ግጭት ተነስቶ በርካታ የሰው ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ የወልቃይት ብጥብጥ በተነሳበት ወቅት በኣማራ ክልል በሚኖሩ ሰላማዊ ተጋሩ ላይ ጥቃት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ሲደረግ ነበር- በተለይ በጎንደርና ባህርዳር ኣካባቢ በርካታ ሲቪልና ሰላማዊ ተጋሩ ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ንብረታቸውን ኣጥተዋል – እሰከኣሁንም ትግራይ ውስጥ በየሳምንቱ በሚሰፈርላቸው እርዳታ የሚኖሩ በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ዜጎች ኣሉ – ስለነዚህ ተፈናቃዮች ሁኔታ ግን በክልሉ መንግስት ብዙም ኣይነገርም (ክልሉ ስለ ተፈናቃዮቹ የማያወራው ነገሮችን ላለማራገብ ይመስለኛ)፡፡ ተፈናቃዮቹ ህይወታቸውን ለማዳን ንብረታቸውን ጥለው ሱዳን ኣገር ድረስ በመሸሽ በሱዳን መንግስት ድጋፍ ወደ ትግራይ የተመለሱ የጥላቻ ጥቃት ሰለባዎች ቢሆኑም በትግራይ ጥላቻ የታወሩ ሰዎች “ወያኔ በኣውሮፕላን ነው ከጎንደር ያስወጣቸው” እያሉ ኣፌዙባቸው፡፡

ባህርዳና ጎንደር ብጥብጡ ጦዞ በነበረበት ወቅት ወሎ ውስጥ ተመሳሳይ ጸረ-ተጋሩ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ከፍተኛ ቅስቀሳ ቢደረግም በወቅቱ ሊሳካ ኣልቻለም – በመሆኑም የትግራይ ጥላቻ ሰባኪዎቹ ወሎዬዎች ላይ ከፍተኛ ቂምና ጥላቻ ኣሳድረው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በወቅቱ ወሎዎች እዚሁ ፌስቡክ ላይ “ፈሪና ሃሞተ-ቢስ” እየተባሉ ሲሰደቡ ነበር፡፡

የጎንደርና ባህርዳር ብጥብጥ ከረገበ በኋላ እነዚህ ሃይሎች ትኩረታቸው ደሴና ወልዲያ ጸረ-ተጋሩ እንቅስቃሴ እንዲደረግ መንቀሳቀስን ላይ ነበር፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያት ወሎ (ደሴና ወልዲያ) ትግራይን ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ጋር የሚያገናኙ ዋናው መስመር በመሆኑ በነዚህ ኣካባቢዎች ጸረ-ትግራይና ተጋሩ ኣመጽ ቀስቅሰህ ትግራይን ከመሃል ኣገር ጋር ማቆራረጥ የሚል ስሌት ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ ቅስቀሳዎች ሲደረጉ ከቆዩ በኋላ በመቐለና ወልዲያ ከለቦች መካከል የእግር ኳስ ግጥሚያ በሚደረግበት ሰኣት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ከጎንደርና ሌሎች ኣካባቢዎች ወልዲያ ድረስ በማስመጣት ግጭትና ብጥብጥ ማስነሳት ችለዋል፡፡ በወቅቱ ሰላማዊ ዜጎች ሞተው የወልዲያ ህዝብ ሰላማዊ ኑሮ ተናግቷል:: የተጋሩ ንብረቶችም በታቀደው መሰረት ኢላማ ተደርገዋል፡፡ ከዛ የቀጠለው ግጭት በተለያዩ ሚድያዎች በመቀስቀስ ለሌላ ግጭትና ሞት ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ ይሄው በእቅዱ መሰረት በሃይማኖታዊ በኣል በጥምቀት ቀን ተፈፅሟል (ቅስቀሳው ከበኣሉ በፊት በግልጽ በኢሳትም ሲደረግ ነበር)፡፡ ይሄ ለረዥም ጊዜ ዝግጅት የተደረገበት ሁከት በሚፈለገው መንገድ የሰው ህይወት ስላጠፋ እንደ ድል ቆጥረውታል – በታቀደው መሰረትም በወልዲያ የሚኖሩ ተጋሩ የጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም “ትግሬዎች ገደሉን ወሎዬ ተነስ” የሚል ተጨማሪና ቀጣይ የእልቂት ዘመቻ ለማካሄድ እንደ ግብኣት ሆኖ እያገለገለ ነው፡፡

ኣሁን ባለው ሁኔታ በቋራ የቀበሌ ምልሻ የተገደለ ሰው ትግሬ ገደለን፣ በክልሉ ፖሊስ የተተኮሰ ጥይት ትግሬ ተኮሰብን፣ መጠጥ ቤት ተጣልተው የተገዳደሉ ሰዎች ትግሬዎች ገደሏቸው ሆኗል ጉዳዩ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በወልዲያ በኩል ወደ ትግራይ የሚያልፉና ከትግራይ የሚመጡ ተሸከርካሪዎች እንዲቃጠሉ፣ ወደ ትግራይ የሚሄደው ኢሌክትሪክ እንዲቆረጥ፣ በኣካባቢው የሚኖሩ ተጋሩ ላይ ግድያና ጭፍጨፋ እንዲካሄድ በግልፅ ኣረመኔኣዊ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡

ይሄ ኣረመኔኣዊ ቅስቀሳና ተግባር ለወልዲያዎችም፣ ለኣማራም ኣጠቃላይ ለኢትዮጵያም የማይበጅ ስለሆነ ሊቆም ይገባል፡፡ በተለይ ደግሞ ኢህኣዴግን መታገልና መጣል የሚፈልግ ሃይል ኢህኣዴግ ወይንም ህወሓትን ይታገል- ትግራይና ሰላማዊው የትግራይ ህዝብን ለቀቅ ያድርግ፡፡ ተጋሩን ኣስጨፍጭፌ ስልጣን ላይ ወጥቼ ኣገር እመራለሁ የሚል ቡድን በደንብ ሊያስብበት ይገባል፡፡ የትግራይ ህዝብ ኣሁን በትግስትና በተስፋ ሁኔታውን ችሎ እየኖረ ነው – ኢትዮጵያ ውስጥ ከሌሎቹ ህዝቦች ጋር እኩል መብቱና ጥቅሙ ተከብሮለት በሰላምና በመከባበር መኖርን እንጂ የህወሓትም ሆነ የኦነግ ስልጣን ላይ መሆን ጉዳዩ ኣይደለም፡፡

ተጋሩን ህወሓትን ለምን ኣትጥሉልንም ወይም እኛ በምንታገለው መንገድ ለምን ኣትታገሉም ብሎ ማስፈራራትና የጥቃት ሰለባ ማድረግ “የፈሪ ዱላ” ነው – ያው የፈሪ ዱላ ደግሞ ሰላማዊ ሰዎችን ይጎዳ ይሆናል እንጂ ዋና ኢላማውን ኣያገኝም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *