የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላምና መረጋጋት የራሱ የሆነ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው

የሚዲያ አጠቃቀም ለሰላምና መረጋጋት የራሱ የሆነ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ዘነበ በየነ ተናገሩ፡፡
በሰላም ጋዜጠኝነት ላይ ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡት ዶክተሩ ግጭቶች በተለያየ ጊዜና አጋጣሚ ሊከሰቱ ይችላሉ ዋናው ነገር ግን ግጭቶቹ የሚዘገቡበት አቅጣጫ በአግባቡ ሊጤን ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ግጭቶችን ማባባስ ሳይሆን ማረጋጋትና ሰላም የመፍጠር ሚና ሊሆን እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
ኃላፊነት በጎደለው የመገሃኛ ብዙኃን ዘገባ በሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ኮሶቮና ዮጎዝላቪያ የተከሰቱ ቀውሶችንም እንደምሳሌ አንስተዋል ዶክተር ዘነበ፡፡
ስለሆነም መገናኛ ብዙኃን የውውይትና የክርክር መድረክ በመሆን ለሰላም መሥራት አለባቸው ብለዋል፡፡
በዓለም ዙሪያ በመገናኛ ብዙኃን ምክንያት የተፈጠሩ ቀውሶች አብዛኞቹ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንደነበራቸውም ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ ረገድም ጥንቃቄ ማድረግና መገናኛ ብዙኃንም ነፃነታቸውን በኃላፊነት መጠቀም አለባቸው ብለዋል፡፡
ይህንን የተናገሩ በትናንትናው እለት በሃገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የሚድያ ኮንፈረንስ ነው!

No automatic alt text available.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *