‘ለድያቆን ዳንኤል ክብረት የተሰጠ መልስ!

በልፍዓተይ ተስፋ የቀረበ

(ዲያቆን ከሆነም ዲያቆን ብላችሁ ጨምሩበት)

በጥያቄኣችሁ መሰረት ተሻሽሎ(ከስድብ ነፃ ሆኖ😂)ድጋሚ ፖስት የተደረገ፦

“ህዝብ ካለ ሃገር ኣለ ፤ ህዝብ ከሌለ ግን መሬት እንጂ ሃገር ኣይኖርም ፤ እናም ሃገር ማለት ሰው ነው።
————————————————————————————
https://www.facebook.com/Orthodoxawit/videos/1070116469786184/

በድፍረት ከጠንካራና የሰላ ትችት እንዳይገጥማቸው ሲሉ “ሃይማኖተኛ” ተብለው ዕድሜ ልካቸውን በሃይማኖት ምሽግ ራሳቸውን ደብቀው እንደ መርከብ ላይ ተንዣብቦ ያለ ተናዳፊ እባብ መንታ ምላሳሶቻቸውን በመዘልዘል ጊዜን እየጠበቁ ኣንድን ጎሳ ኣልያም ታዋቂ ሰውን እነሱ ወዳሉበት ዝቅተኛው የ70 ደረጃ ረድፍ ጎትተው ለማንሸራተት ከሚዳዱ በርከት ያሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስትያናችን ጉያ ጉንዳኖች መካከል ኣንዱ ዳንኤል ክብረት ነው።

ለዚሁ ማረጋገጫየ ዳንኤል ክብረት ሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ቀርቦ “እኔ የፖለቲካ ፀሃፊም የሃይማኖት ሰባኪም ነኝ” ብሎ በኣንደበቱ ተናግሯል።

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን እና የማ/ቅርሱሳን ልዩነት የተምታታበት የዘመናችን ኣጨብጫቢ ወይም “ተዋህዶ ኦርቶዶክስ መሳይ” ምእመን በተለይም ወጣቱ የዳንኤል ክብረት እና የማ/ቅርሱሳኑ ተከታይ እንጂ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ተከታይ ኣለመሆኑን ገና የባነነ ኣይመስለኝም። ምክንያቱም የቤተክርስቲያኒቱ ቀዳሽ ፤ ወዳሽ ፡ ገዛች ፡ኣቁራቢ ፡ ኣሳሪ እንዲሁም ፈቺ ቅዱሳን ኣባቶችን ብፁኣን ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ቅዱስ ወብፁእ ፓትሪያርኩ ፤ መለኮታው ቃል የተፃፈበት ቅዱስ ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ማክበሩን ዘንግቶ የማህበሩን ኣፈቀላጤ ጎረምሶችን የሚያከብር የከሰረ ትውልድ እያስተዋልኩኝ ስለሆነ። ይሄ ከምክር እንጂ ከስድብ ኣትቁጠሩብኝ።

የሚያሳዝነው የዘንድሮ ተማሪዎች የዪኒቨርስቲ ወይስ የማ/ቅርሱሳን ተማሪዎች መሆናቸውን ግራ ትጋባለህ። ቀዳሚት እና ሰንበትን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲያቸው የሰጣቸውን የማጥኛ ጊዜ ለማ/ቅርሱሳን የዘረኝነት ቲኦሎጂ ክፍለ ጊዜ ማዋላቸው በሃገር ሃብት (ሻይና ዳቦ/ሩዝ) ጥናትና ምርምር ላይም ሆነ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥንታዊ ዶግማ እና ቀኖና ላይ(የመፅሃፍ ቅዱስ የሂይወት ቃል ሳይሆን የተስፋ ገ/ስላሴ ድርሰቶች ሲያጠኑ ይውላሉ) ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰ ለመሆኑ እርግጠኛ ነኝ።

እስኪ ወደ ሓተታው እንሂድ፦
===============

ሰው ጥያቄውን ኣልያም ሓተታውን በውል ሳይረዳ እንዴት 7 የዓለማችን ኣህጉራት እየዞረ ይዋትታል?😂

(ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ማስተዋልን ስለሚጠይቅ ሰከን ባለ ኣእምሮ ቢነበብ ይመረጣል)

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ፦
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

“ለኔ ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ነበር ያሉት። ይህንንም ጠ/ሚሩ ሲያብራሩ “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው ስል በኣከባቢያችን ያሉ ከኣባት እናት እህት ወንድም ኣጎት ኣክስት እያለ እስከ መላው ህዝባችን እያለ ይሰፋል። ለኔ ሃገር ማለት ወንዙ ተራራው ብቻ ኣይደለም ፤ ወንዙ ተራራውማ ሁሉም ኣይለያዩም ፤ ሰው ግን ከሰው ፤ ህዝብም ከህዝብ ፡ በባህል ፤ በእምነት ፤ በስርዓት ፤ በቋንቋ እና በህግ/በስርዓት ይለያያል። ጀግና ህዝብ ኣለ ። የጀግና ህዝብ ተራራ እንጂ ለብቻው ጀግና የሆነ ተራራ የለም። የጀግና ህዝብ ወንዝ ኣለ ፤ ወንዝ በራሱ ግን ጀግና ሊሆን ኣይችልም ፤ የወንዝ ጀግናም የለም። እናም ህዝብ ካለ ሃገር ኣለ ፤ ምድር ኖሮ ህዝብ ከሌለ መሬት ነው ያለው ፤ ኣልያም ህዝብን ሳያከብሩ መሬቱን ማክበር ለኔ የሃገር ፍቅር ሊሆን ኣይችልም” ነበር ያሉት ጠ/ሚሩ።

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ “ኣገር ማለት ሰው ብቻ ነው” ብሎ የሚያምን ጅላጅል እንዳልሆኑም ሊሰመርበት ይገባል። ለዚሁ ትልቁ ማረጋገጫችን የባድመ ፤ የፀሮና እና የሶማሊያ ወረራና የወረራ ስጋት ለመከላከል የተደረጉ ጦርነቶች ምስክሮች ናቸው። ዳንኤል ግን ጠ/ሚሩ “ኣገር ማለት ሰው ብቻ ነው” ብሎ እንደሚያምን ለማስመሰል ያልሞጫጨረው መጣጥፍ የለም። ዳንኤል በየFM የራዲዮ ጣብያዎች ፤ በየ TV ሾው ፕሮግራሞች “ሃገር ማለት መሬት ነው” ሲል ተደምጧል ፤ ታይቷል ፤ መፅሃፍም ኣሳትሟል። እሱም ብቻ ኣይደለም ሌሎቹ የኣማራ የጠነባ ፖለቲካ ኣቀንቃኞችን ሃሳብም በተደጋጋሚ በግላጭ ሲያንፀባርቅ ይታያል።

ኣስቡት እስኪ የተለየ የመሬት ኣቀማመጥ እና የመሬት ካርታ ያላትን ታላቋ ኢትዮጵያን የሚመራ ሰው ፤ ለዛውም ባለ ምጡቅ ኣእምሮ መሪ “ኣገር ማለት ሰው ብቻ ነው” ብሎ ተናገረ ተብሎ በኣንድ ዲያቆን ነኝ ባይ ዳንኤል ክብረት የውሸት መጽሃፍ መፃፍ የህልም ዳውላ ሸክም ከመሆን የዘለለ ፋይዳ ይኖረው ይሆን??? ለትእዝብትም ይዳርጋል።

ዳንኤል እንደ ክርስቲያን ዲያቆን ህዝብን ከህዝብ የሚያቀራርብ ስራ ከመስራት ይልቅ ህዝብን ከህዝብ የሚያለያይ ስራዎችን በመሞጫጨር ይታወቃል። ከጠባጫሪ ስራዎቹ መካከልም፦

ኢትዮጵያን እናዋልዳት ፤ ትእግስታችን ወሰን ይኑረው ፤ ዝሆኖቹ (ኣማራነትን ለማጉላት) ፤ ውሾቹን ተው በሏቸው (ተጋሩን ለማጠልሸት) ፤ ጊንጥ ፤ የሚከራዩ ኣማት ፤ የሰርቆ ኣደሮቹ ስብሰባ ፤ …ወዘተ ህዝብን በተለይም ደግሞ ተጋሩን ለማንኳሰስ ከፃፋቸው መጣጥፎቹና መፃህፍቶቹ ጥቂቶቹ ናቸው። የሚገርመው ሁሉም ፅሁፎቹ በreferrence ድርቅ የተመቱ ተረታዊ መጣጥፋዊና ህልማዊ ድርሰቶች ናቸው። ዳንኤል ለክፋትና ለዘረኝነት የተፈጠረ እንክፍ መልኣክ መሳይ ጭራቅ ነው ብል ማንነቱን መግለፅ እንጂ መስደብ ኣይደለም።

ደግነቱ የሱ የሽሙጥ ስድቦች ኣንብበው በቀላሉ የሚረዱ ሰዎች ጥቂቶቹ ናቸው። በዚህ ምክንያትም ዳንኤል ከኣድናቆት በቀር ለከፋ ትችት ሲዳረግ ኣይስተዋልም። የሚያውቁት ግን በደምብ ያውቁታል።

እውነታው እና ተጨባጭ ጉዳዩን እንይ፦
======================
ጀግና ሰው ፤ ኣልያም ጀግና ህዝብ ከሌለ መሬት በራሱ ራሱን ለማስጠበቅ እንደምን ይዋጋል?
እየኖርንባት ያለቺውን ዓለማችን እኮ 1 ናት ፤ የተለያየች ኣይደለቺም። ስለሆነም በዚህች በምንኖርባት ኣንዲት መሬት ላይ ከ260 በላይ የተለያዩ ሃገራት የፈጠረው ሰው ነው እንጂ መሬት በራሷ ጊዜ በ260 ተሰነጣጥቃ ኣይደለም። እነዚህን ሃገሮች በሚፈልገው ካርታ እና ድምበር መፍጠር የቻለው ሰው ነው። ይህም ሰው ሃገር ተባለ😂 እናም የተለያዩ የዓለማችን ሰዎች በሚስማማቸው መንገድ ተጠቅመው ካርታ እና ድምበር ኣበጅተው የየራሳቸው ግዛት ፈጠሩ። ይህም ማለት ህዝብ ካለ ሃገር ኣለ ፤ ህዝብ ከሌለ ግን መሬት እንጂ ሃገር ኣይኖርም። ስለዚህ የጠ/ሚሩ ኣነጋገር ከዚህ የሚነሳ ነው።

ወደ ሃይማኖት እንምጣ፦
#############
ኣምላክ በእለተ ሰንበት ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ። በዚህ ብቻ ኣላበቃም ለሰው የሚያስፈልገው ነገር በሙሉ እስከ እለተ ሓሙስ ፈጠረለት። ከዚህ በኋላ ይህንን ፍጥረት በስልጣኑ ለሚጠቀመው እና በእግዚኣብሄር ልብ ላለው ፍጥረቱ ለሆነው ሰው ይቸረው ዘንድ በእለተ ዓርብ ሰውን ፈጠረ። ሰዎችም ከኣዳም በኋላ ቁጥራቸው ስለጨመረም ብዙ ሃገራት መሰረቱ። ቁጥራቸው ሳይጨምር ግን 1 ዓለም የሆነች የኣዳም ሃገር ብቻ እንጂ ብዙ ሃገራት ኣልነበሩም። ኣዳም ከመፈጠሩ በፊት 5 ቀናት በቀር ዓለም ለኣዳም ሃገሩ ነበረች።

ስለሆነም ሃገር ማለት ሰው/ህዝብ ያለው መልከዓ ምድር እንጂ ራሱ መልከዓ ምድሩ ብቻውን ኣይደለም። ምክንያቱም ዓለም ከሰንበት እስከ ሃሙስ(ኣዳም ከመፈጠሩ 5 ቀናት በፊት) ስትፈጠር ኣዳም ገና ስላልተፈጠረ ምድር እንጂ ሃገር ኣልነበረችም።

እግዚኣብሄር ምድርን ስለ ሰው ፈጠረ እንጂ ኣንተ ኣጉል ሃይማኖተኛ ኣጉል ፖለቲከኛ ኣጉል ዘረኛ የሆንከው ዳንኤል እንደምትለው ሰው ስለ ምድር ኣልተፈጠረም።😂 እንዲያማ ቢሆን ኖሮ መላእክትን ጨምሮ ከሰማይና ምድር እንዲሁም ከሰው በፊት ለፈጠራቸው ፍጥረታትም ኣስቀድሞ ምድርን በፈጠረላቸው ነበር።😂

“የመላእክት እና የፃድቃናት ሃገራቸው ሰማይ ነው” ሲባል ኣልሰማህም? ይህ ማለት “ሃገር” ከመላእክት እና የፃድቃናት(ሰዎች) ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ቁልጭ ኣድርጎ ያሳያል። መቼም ሰማይ የሚባል ምድር ኣለ ብለህ ኣትከራከርም።

ኣንተ የነፍጠኞች ስህተትን ለማከናነብ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰጠችህን የቤተክህነት ፀጋ ወደ ጎን ክደህ “ሃገር ማለት መሬት ናት” እያሉ መሬቷን እንኳ ሳያስጠብቁ ለጣልያን ፤ ለፈረንሳይና ለእንግሊዝ ከቸረቸሩ የባንዳ መሪ ኣያቶችህ ጎን መቆምህ ካንተ የማይጠበቅ ኣይደለም። 😂

ለመሆኑ በቤ/ክርስቲያናችን ኣንድን ሰባኬ ወንጌል “ኣሶሳ ኣህጉረ ስብከት ሄደ” ሲባል ምን ማለት ነው?

ኣሁንስ ገባህ???😂

“ኣህጉር” ማለት ህዝብ ማለት ኣይደለም? እናም ሰባኪው ህዝቡን እንጂ መሬቱን ሊሰብክ ኣይሄድም!😂

“ኣህጉር” ማለት ህዝብ ህዝብ ያለበት ቦታ ማለት ነው።

ኣህጉረ ስብከት ለመጀመርያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችንን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ዓለምን ዕጣ በዕጣ ተከፋፍለው ለማስተማር በወጡ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ይመቻ ፤ አይመችም ሳይሉ በተሠማሩበት ሀገረ ስብከት ገብተው አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል ፤ ምእመናንን አስተምረው በማጥመቅ ፤ ካህናትን እና ዲያቆናትን በመሾም የወንጌልን ቃል ለዓለም አዳርሰዋል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ኣህጉረ ስብከቱ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊው በታናሽ እስያ ኣህጉረ ስብከቱ ፤ ቶማስ በሕንድ ኣህጉረ ስብከቱ ፤ ማርቆስም በእስክንድርያ ኣህጉረ ስብከቱ ፤ የሠሩት ሥራ ለዚህ ማስረጃችን ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወንጌላውያን ወደነዚህ ኣህጉራት ሲበታተኑ ህዝብን ለመስበክ እንጂ መሬትን ለመስበክ ኣይደለም። ሰው እንጂ መሬት መቼ ሃጥያት ሰራ እና !!!

“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራስዋን አህጉረ ስብከት መመሥረት የጀመረችው ከራስዋ ልጆች መካከል ፓትርያርክ ባገኘች ጊዜ ሲሆን በ1943 ዓም የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ አቡነ ታዴዎስን ለጎሬ ፣ አቡነ ገብርኤልን ለወሎ ፣ አቡነ ማርቆስን ለኤርትራ ፣ አቡነ ፊልጶስን ለኢየሩሳሌም፣ አቡነ ጎርጎርዮስን ለከፋ ጳጳሳት አድርገው ሾመው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ቆይቶም በ1948 ዓ.ም ትግራይ በሀገረ ስብከትነት ተቋቁሞ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ተሾመውበታል፡፡ ” ይላል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ» በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደገለጡት። ይህም የሚያሳየን “ኣህጉር” ማለት ምእመን/ህዝብ ማለት እንደሆነ ነው። በዓለማችን ህዝብ የሚኖርባቸው 6 ኣህጉራት እና ህዝብ የማይኖርበት 1 የብስ (ኣንታርክቲካ) ኣለ።

እናም ከላይ በምሳሌው እንደምንረዳው “ኣህጉር” ማለት ህዝብ ያለበት ቦታ ማለት ነው። ኣህጉረ ስብከቱ ለማስፋፋት 4ቱም ወንጌላውያን ይሁኑ የዘመናችን ሰባኪዎች ወደ ኣንታርክቲካ ኣልሄዱም። ለምን? ኣንታርክቲካ ሃገር ስላልሆነ። ለምን ሃገር ኣልሆነም? የሰው ልጅ ኣይኖርበትም😂

ሌላ ምሳሌ ፦

ኣንድ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ህንፃ(ቤቱ/ግምቡ) በውስጡ ታቦት ከሌለው ቤተክርስቲያን ብለን እንጠራዋለን?(ኦሪት ዘኅልቁ 22፥31፤ ማር11፥17፤ ኢሳ 56 ፥ 7፤ ኤር 7፥11 ፡፡) ላይ ተጽፏል።😂

ኣንድ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ህንፃ(ቤቱ/ግምቡ) በውስጡ ታቦት ከሌለው ቤተክርስቲያን ብለን ኣንጠራውም። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ህንፃ ቤተክርስቲያን ብለን የምንጠራው በውስጡ ታቦት/ታቦታት ሲኖሩት ብቻ ነው።

ልክ እንደ ቤ/ክርስቲያኒቱ ሁሉ ኣንድ ሃገር ሃገር ብለን የምንጠራው በውስጡ ሰው/ህዝቦች ሲኖሩት ነው።

ኣሁንም ሌላ ምሳሌ፦

እስራኤል ማለት የመሬት ስም ሳይሆን የሰው ስም ነው። እስራኤል ማለት የእግዚኣብሄር ህዝብ ማለት ነው። መሬቱም የእስራኤላውያን (የ20ዎቹ ነገዶች) ነው። እናም ሃገሩ እስራኤል ነው። እስራኤልም መሬት ሳይሆን ህዝብ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ያዕቆብን ያዕቆብ ብሎ የጠራበት ዘመን ነበረ። ከኪዳን በኃላ ግን “እስራኤል” ብሎ ጠራው። ልብ በሉ ኣንባብያን ፦ እግዚአብሔር ያዕቆብን እንጂ “እስራኤል” የሚኖርበት ምድር/መሬቱን ኣይደለም “እስራኤል” ብሎ የጠራው። ይህንንም ቃል ከሱ ልጆች ከይስሀቅና ከያእቆብ ጋር አጸናው። ያእቆብንም ባርኮት ስሙንም ካሁን ቡሀላ “እስራኤል” ትባላለህ ብሎ ስም ኣወጣለት።(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 25) ለዚህም ነው ኤስራኤላውያን ምንም እንኳ መሬታቸው ተወርሶና ጠፍቶ ከሞት የተረፉት ሰዎቹም ወደ ተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ብትንትናቸው ቢሰደዱም ሰዎቹ /ኤስራኤላዊያኑ ከየትም ተሰባስበው ዳግም ሃገር ሆነው ሃገራቸውን የመሰረቱት።

ኣሁንም ሌላ ምሳሌ፦

“ኣኽሱም” ከ ንጉስ ኣኽሱማይ የተገኘ ስያሜ እንጂ የኣክሱም ምድር ስያሜ ኣልነበረም።

“ኢትዮጲስ” ከ ንጉስ ኢትዮጲስ የተገኘ ስያሜ እንጂ የኢትዮጵያ መሬት ስያሜ ኣልነበረም።

“ሃገረ ኣግኣዝያን” ከኣግኣዝያን/ትግራይ ህዝብ የተገኘ ስያሜ እንጂ እነሱ ይኖሩበት የነበረ ስያሜ ኣልነበረም።

ወ………………..ዘ………………..ተ

እንደመጣላችሁ ትሰብካላችሁ ፤ ደስ ሲላችሁ ከሰባኪነት ወደ ፖለቲከኛነት ተለውጣችሁ የሰው ስም ታጠፋላችሁ፤ በጣም እምትገርሙና እምታሳፍሩ ፍጡራን ናቹህ። ይህኔ ይህንን ያንተው እንቶፈንቶ መጽሃፍ ቢጤ የከተበው ትግራዋይ ዲያቆን ቢሆን ኖሮ ያ እንክፍ ማህበርህ “ተሃድሶ፤ወያኔ” የሚል ታፔላ ይለጥፍበት ነበር። ምነው ታድያ ኣንተ ላይ ኣፉን ለጎመ???😂

ኣገር ካለሰው ኣገር እሚባል ቢሆን ኑሮ ኤስራኤል እንደ ኣገር ለዘመናት ጠፍታ ነበር አይደል እንዴ? እና ያኔ እስራኤል እምትባል አገር ነበረች? አልነበረችም😎 ለምን ቢባል ህዝቦቿ በዓለም ተበታትነው ስለነበር እስራኤል እምትባል ኣገራቸውም ጠፋች። እዚህ ላይ ልብ ልትሉት የሚገባ ነጥብ ህዝቦቿ በዓለማት ተበታተኑ እንጂ ምድሩ የትም ነቅነቅ አላለም። 😎 ኣሁን ኤስራኤላውያን እየኖሩበት ያለው ምድር ጥንት ከዕለተ ፍጥረት ጀምሮ የነበረ ምድር ነው። ከሂህም ቡኋላ የእስራኤል ህዝቦች ፖላስታይን ላይ መሰባሰብ ስለነበረባቸው ኤስራኤላውያን ይህን ሲያደርጉ ዓለም “ኤስራኤል” ብላ እውቅና በመስጠት አገር ተፈጠረች 😎 ስለዚሀ ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው።

እስኪ ወዳንተ ቀሽም ጥያቄዎች እንሂድ፦
======================
1) ሃገር ማለት ሰው ከሆነ ይሄ የኔ ክልል ፤ ጎጥ እና መንደር ከየት መጣ?ለሚለው ጥያቄህ ፤ ሀገር ማለት መሬት ከሆነስ የሰው ልጅ የሌለው ባዶ መሬት ይሄ የኔ ክልል ፤ ጎጥ እና መንደር ነው የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ኣካል ያለ ይመስልሃል? ድድብና #1 ነው። ይህንን ጥያቄ ያስነሱት ግን ሰዎች እንጂ ባዶ መሬትማ ብቻዋ የኣዳም ሃገር ነበረች። 😂

2) ሃገር ማለት ሰው ከሆነ የተለየ ድምበር እና ካርታ ለምን ኣስፈለገ? የሚለው ጥያቄ በሌላ ኣነጋገር ኤርትራን እንደሃገር የተለየ ድምበር እና ካርታ ኣዘጋጅተው ኤርትራ ያሰኟት ህዝቦቿ ናቸው። ኤርትራውያን ባይኖሩ ኖሮ መሬት እንጂ ከስሟ ጀምሮ የተለየ ድምበር እና ካርታ ያላት ሃገር ኣትሆንም ነበር። ምክንያቱም ኤርትራ ፤ ኢትዮጵያ ፤ ኣሜሪካ ወዘተ የሚባል ስም ለመሬቱ የተለየ ድምበር እና ካርታ ኣዘጋጅተው የሰጡት የነዚሁ ኗሪ ሰዎች እንጂ መሬቱ በራሱ ለራሱ ያወጣው የመጠርያ ስም ይሁን የተለየ ድምበር እና ካርታ የለም ፤ መሬቱ በራሱ ይህንን ማድረግ ስለማይችል። ይህም ማለት መሬቱ ወደ ሃገርነት የተቀየረው በውስጡ ባሉት ሃገር ለመሆን በወሰኑ ሰዎች ኣማካኝነት ነው። ለምሳሌ በኣማርኛ ኣላውቅም በትግርኛ “ሃገር ተጎቢኣ” ማለት በተለየ ድምበር እና ካርታ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች በከፍተኛ ሁኔታ ተጎዱ፤ ሞቱ ለማለት እንጂ መሬቱ ተገለባበጠ ለማለት ኣይደለም። የነነዌ ሰዎች/ህዝቦች ነነዌ ህዝቦቿ ስለተቀጡባት “ነነዌ በመቅዘፍት ተቀጣች” እንላለን እንጂ የነነዌ መሬት ተቀጣ ኣንልም። ባጠቃላይ 1 ሃገር የሚቀጣውም የሚሸለመውም ስለህዝቡ/ሃገሩ እንጂ ስለ ምድሩ ኣይደለም።😂

ሌላ ምሳሌ እኤኣ የ2016ቱ የጃፓኑ ከባድ ዝናብ የቀላቀለ ኣውሎ ንፋስ የፉኩሺማ የኑክሌር ማብላያ ጣብያው በመበላሸቱ ምክንያት ለብዙ ጃፓናውያን ህልፈተ ህይወት ምክንያት በመሆኑ የዓለም ብዙሃን መገናኛዎች “ጃፓን የሞት ድግስ ኣፋፍ ላይ ናት” ሲሉ ዘግበዋል። ታድያ ያኔ የሞት ድግስ ኣፋፍ ላይ የነበረቺው ጃፓን መሬቷ? ወይስ ህዝቧ? መቼም በፖለቲካው ዓለም ህዝብ ካልሆነ በቀር መሬት ኣይሞትም። የሞት ድግስ ኣፋፍ ላይ የነበሩት የጃፓን ህዝቦች/ሰዎች እንጂ የጃፓን መሬት ኣልነበረም እና።

ሰው የትም ይኖራል። ሰው የትም ሲኖር ግን የሚኖርበትን ህዝብ ባህል እምነት እና ህግ ኣክብሮ ነው። ልብ በሉ ሰው የትም ሲኖር ግን የሚኖርበትን ህዝብ ባህል እምነት እና ህግ ኣክብሮ እንጂ መሬቱን ኣክብሮ ኣይደለም። የሚኖርበትን ህዝብ ባህል እምነት እና ህግ ኣክብሮ ማለት የሃገሪቱን ባህል እምነት እና ህግ ኣክብሮ ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ የህዝቡ ባህል እምነት እና ህግ ኣከበረ ማለት ነው። ይህ ባህል እምነት እና ህግም የሰው/የህዝብ እንጂ የመሬቱ ኣይደለም።

ለምን? ቢባል እነዚህ ህዝቦች በሌላ ኣገር ህዝቦች ከገዛ ሃገራቸው ቢወገዱ የሃገሪቱ/የህዝቡ ባህል እምነት እና ህግ በኣስወጋጆቹ/ወራሪዎቹ ባህል እምነት እና ህግ ይተካል። ይህ ማለት የሃገሪቱ ባህል እምነት እና ህግ ተተካ ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ፅንሰ ሃሳብ መሰረት መሬት የራሱ ባህል እምነት እና ህግ የለውም። ሰው ግን የራሱ የተለየ ባህል እምነት እና ህግ ኣለው ። እናም ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ፦”ለኔ ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ማለታቸው ለእንደነ ዲያቆን ይሁን ዳንኤል ክስረት የመሳሰሉት ባለ ሚጢጢዬ ጭንቅሎ በመክበዱ ባይገርመኝም ይህንን ፅንሰ ሃሳብ ሳይረዱ መጽሃፍ ለመሞጫጨር መፍገምገሙ ግን ገርሞኛል😂 ምክንያቱም እንደነ ዳንኤል ክስረት የመሳሰሉት ባለ ሚጢጢዬ ጭንቅሎዎች በሃገራችን በርካታ እንደሆኑ ከመጽሃፉ ዋጋ ለመረዳት ይቻላል።

3) ሃገር ማለት ሰው ከሆነ ብሄራዊ መዝሙሩ ስለ ድምበርና ስለካርታ ለምን ያወራል? ያልከው
የኣሁኑ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄራዊ መዝሙር፦

“የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ፤
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ፤
ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት፤
በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት፤
መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን፤
ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን፤
ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት፤
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት፤
እንጠብቅሻለን አለብን አደራ፤
ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።”😂

ይላል። ታድያ የቱ ላይ ነው ብሄራዊ መዝሙሩ ስለ ድምበርና ስለካርታ ያወራው? የዲያቆን ውሸታም!!!

“የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ፤
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ፤”

ይሄ ስለ ዜጎች ክብር እንጂ ስለ ድምበርና ስለካርታ ኣያወራም። እናም “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር ኣይጋጭም።😂

“ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት፤
በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት፤”

ይሄም ስለ ህዝቦች/ዜጎች ክብር ፤ ፍቅር እና ኣንድነት እንጂ ስለ ድምበርና ስለካርታ ኣያወራም። እናም “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር ኣይጋጭም።😂

“መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን፤
ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን፤”

ይሄም ስለ ዜጎች ጀግንነት ፤ ስብእና/ክብር ፤ የስራ ትጋት እንጂ ስለ ድምበርና ስለካርታ ኣያወራም። እናም “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር ኣይጋጭም።😂

“ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት፤
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት፤”

ይሄም ቢሆን ስለ ዜጎች ባህልና ወግ ፤ ቅርስ እንዲሁም የተፈጥሮ ፀጋን እና ስለ ህዝቡ ጀግንነት ይናገራል እንጂ ስለ ድምበርና ስለካርታ ኣያወራም። እናም “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር ኣይጋጭም።😂

“እንጠብቅሻለን አለብን አደራ፤
ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።”

ይሄም ቢሆን ስለ ዜጎች ለሃገራቸው ክብር የገቡት ቃል/ኣደራ የሚያጠይቅ እንጂ ስለ ድምበርና ስለካርታ ኣያወራም። እናም “ሃገር ማለት ከምንም በላይ ሰው ነው” ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጋር ኣይጋጭም።😂

ስለዚህ ሃገር ማለት ሰው ከሆነ ብሄራዊ መዝሙሩ ስለ ድምበርና ስለካርታ ለምን ያወራል? ያልከው ፈጥረህ እና ዋሽተህ ነው። የዲያቆን ቀጣፊ ውሸታም ነህ ማለት ነው😂

4) ሃገር ማለት ሰው ከሆነ ኣንድ ሰው ለምን ቪዛ እና ፓስፖርት ያስፈልገዋል? ያልከው ቪዛ እና ፓስፖርቱ የሚጠየቀው ለመሬቱ ሳይሆን ተጓዡ ወደሌሎች ዜጎች/ሰዎች/ህዝቦች እየተቀላቀለ ስለሆነ ለሱ መለያ/መታወቂያነት ነው። ቪዛው እና ፓስፖርቱ እኮ ተጓዡ ለሚኖርበት መሬት ሳይሆን ለራሱ ለተጓዡ ሰውዩ የተሰጠ እና ወደሚጓዝበት ሃገር/ሰው/ህዝብ ሲደርስም ኣዲስ ለሚረግጠው መሬት ሳይሆን ኣዲስ ለሚቀላቀለው ሃገር/ሰው/ህዝብ ነው የሚያሳየው። እናም ቪዛ እና ፓስፖርት ለሰው/ለሃገር እንጂ ለመሬት ኣልተበጀም።😂

ለምሳሌ ኣንድ የከብት እረኛ የብዙ ሰዎች ከብት የሚጠብቅ ከሆነ ከብቶቹ የማን የማን እንደሆኑ ለመለየት ወይ ጆሮኣቸውን ይበሳቸዋል ፤ ወይ መልካቸውን ይለየዋል ፤ ኣልያም የራሱ ስያሜና ምልክት ሰጥቶ ያውቃቸዋል። የዚህ እረኛ የሚያግዳቸው ከብቶቹን መለያ የሚጠቀምበት ከብቶቹን ኣንዱ ከሌላው ከብት ለመለየት እንጂ ፤ ኣንዱን የሚያውልበት(የሚያበላበት የግጦሽ ቦታ) ከሌላው ጊዜ ከሚያበላበት የግጦሽ ቦታ ለመለየት ኣይደለም።ልክ እንደዚሁ ቪዛ እና ፓስፖርትም ለሰው/ለሃገር እንጂ ለመሬት ኣልተበጀም። (ኢትዮጵያዊው ከኣሜሪካዊው ሰውየ/ዜጋ ለመለየት እንጂ የኢትዮጵያ መሬት ከኣሜሪካ መሬት ለመለየት ኣይደለም።) ለዚህም ነው “ሃገር ማለት ሰው ከሆነ ኣንድ ሰው ለምን ቪዛ እና ፓስፖርት ያስፈልገዋል?” ያልከው ጥያቄ “ሰው ጥያቄውን ኣልያም ሓተታውን በውል ሳይረዳ እንዴት 7 የዓለማችን ኣህጉራት እየዞረ ይዋትታል?” ብየ የመለስኩልህ። 😂

በእርግጥ ኣንተ የጠ/ሚ መለስ ንግግር ለመረዳት ጭንቅላትህ 1ሺህ ኪሎ ኣዮዲን ይሸከም ይሆናል እንጂ ኣይረዳህም ፤ ሊገባህም ኣይችልም። እንዴ እድሜ ልክህ ቤ/ክ ተምረህ ቃለ እግዚኣቢሄር ሊገባህ ያልቻለ ሰውየ በምን እሳቤ ነው ዓለም የመሰከረለትን የባለ ምጡቅ ኣእሙሮ ባለቤት የሆነውን ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ንግግር ሊገባህ የሚችለው???😂

የእግዚኣብሄር እና የምንሊክ ልዩነት የተምታታብህ ሰውየኮነህ😂

እንዴ ሲጀመር ዳንኤል ኣንተኮ ባህላዊ/ዘልማዳዊ እንጂ ምሁራዊ/ፕሮፌሽናል ፀሃፊ ኣይደለህም።

ሰለ መለስ ዜናዊ ለማውራት ፈልገህ ከሆነ የመለስን አእምሮ ብሰለት የሚመለከታቸው ምርጥ የሆኑ የዓለም ኤኮኖሚሰቶች ፤ የአለም መሪዎች፤ የዓለም ፖለቲካ ሳይንትሰቶች ፤ የዓለም የተፈጥሮ ኣዋቂና ተማራማሪዎች ወዘተ ፤ እረ ሰንቱ ተብሎ ለመዘረዘር በሚያዳግት ሁኔታ እምቅና ምጡቅ ብቃቱን ሰለገለፁ እንደ ኣንተ ዓይነቱ የአንድ የመንደር አዋቂና የአሉባልታ ወሬ አድማቂ ምሰክርነት አያሰፈልገውም። መለስ ዜናዊ ያለፈው የ5500 ዘመንእና የመጭው ዘመን የዓለም ታሪካዊ ፤ ፖለቲካዊና ሳይንሳዊ ቅምርታን በብሩህ ኣእምሮው ያየ እና የራሱን ዓሻራ ኣኑሮ ያረፈ የተነበየ ባለ ምጡቅ ኣእሙሮ ፍጥረት(ኣብሪ ኮከብ) ነው።

ኣንተግን በ100 ዓመት ኋላቀር የምንሊክና በኃ/ስላሴ ተረት ታጥረህ ያለፈውን እና መጭውን የዓለም ሁኔታ ማየት የተሳነህ ድኩም ሰው ነህ። የምታስቀምጣቸው ሪፈረንሶችህ እኮ የሚከተሉት ናቸው፦

በውል ባይታወቅም ተብሎ እንደሚገመት ይገመታል😂

መርጌታ እከሌ ይገመታል ብለው ግምታቸውን ኣስቀምጠዋል😂

ማ/ቅርሱሳን በስምኣ ፅድቅ ኣስፍሯል😂

ይባላል ይባል ነበር፤😂

ኣሉ😂 …………………….ወ ዘ ተ

እና ኣሁን የመሬት እና የሰው/ህዝብ ልዩነት ግልጽ የሆነላችሁ ይመስለኛል።

ለማጠቃለል፦

የማ/ቅርሱሳን ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት ሙት ወቃሽ ነው። ለምሳሌ መለስ እንዳረፈ ሳልስትሳይሞላው “2004 ዓ/ም የተማርንበትም የተማረርንበትም ዓመት ነው” በሚል ኣርእስት የፃፈው ፅሁፍ ይህንን የሙት ወቃሽነቱ ያሳበብቅበታል። በክርስትናም በእስልምና ህግም ይሁን እምነት ሙት እንደማይወቀስ እና ነውርም እንደሆነ ደጋግመን ሰምተናል። ይህ ድርጊት ከአንድ የሃይማኖት ሰው ነኝ ብሎ ራሱን ከሚቆልል ከንቱ ፍጥረት ሙትን መውቀስ ለምን ተደጋገመ? ብለን ያልን እንደሆነ ይህ ከጀርባው ያሉት ኣለቆቹ ስሜት ነው ያንፀባረቀልን። ለማንኛውም ሁሉም የዳንኤል ፁሁፎቹ የተረት እና ምሳሌ ስለሆኑ ለህፃናት እንጂ ለአዋቂዎች አይመጥኑም። በነገራችን ላይ አንድ ሰው ሃይማኖተኛም ፖለቲከኛም እንዴት ሊሆን ይችላል?

እናም የሆነ ባዶ መሬት ወይም ሰው ኣልባ መሬት ሃገር የሚሆነው ሰው ሲሰፍርበት ነው። ሰው ያልሰፈረበት ኣልያም ሰው ኣልባ መሬት ሰው ኣልባ መሬት እንጂ ከቶም ሃገር ሊሆን ኣይችልም።

ለምሳሌ፦

ኣንታርክቲካ ሃገር ኣይደለም። ባዶ መሬት ወይም ሰው ኣልባ መሬት ግን ነው። ወይም ደግሞ ሰው ኣልባ ኣህጉር ነው። ሃገር የሚያሰኝ ነገር የለውም።ሃገር የሚያሰኘው ነገር ሰው ነውና።

በመጨረሻም ፦

ለኔ ልማታዊ ህዝብ ከሃገር በላይ ነው ፤ ይህ ህዝብ ሲኖር ሃገር ትከበራለች ፡ ትፈራለች። ይህ ህዝብ በሌለበት የሃገር ልማትና ክብር የማይታሰብ ነው።

እንደነ ዳንኤል ለመሳሰሉት ለእምቦጮች ግን ህዝብ ከሃገር በታች ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *