የኤርትራውያን ያልተቋጨ ስቃይ!

እስራኤል ከሀገር አልወጣም ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞችን አሰረች ::

የእስራኤል መንግሥት በሀገሪቱ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳና ኡጋንዳ በመላክ ሙሉ በሙሉ ከሀገር የማስወጣት እቅድ እንዳለው ተግልጿል። እስካሁን ባለው 600 የሚሆኑ ስደተኞች ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ሲሆን ወደ 35 ሺ የሚሆኑ ስደተኞችም ከሀገር የመባረር አደጋ ላይ እንደሆኑ አንድ የእስራኤል የስደተኞች መብት ድርጅት አስታውቋል።
ስደተኞቹ ሆሎት ከሚባለው የማቆያ ማዕከል የተወሰዱ ሲሆን በማእከሉም የረሀብ አድማ መነሳቱ ታውቋል። የእስራኤል መንግሥት በጥር ወር አካባቢ ስደተኞቹ ከሀገር እንዲወጡ ቀነ-ገደብ ያስቀመጠ ሲሆን አለበለዚያ ግን እስር እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ስደተኞቹ እሰራኤልን በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ ለቀው ለመውጣት ከተስማሙ 3500 ዶላር ይሰጣቸዋል ተብሏል።

ግዕዝ ሚዲያ
ለቀዳሚነት እንሰራለን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *